ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ለዕለቱ የተመረጠ ጽሑፍ
enllaç=
page=1


የሾላ ዛፍ

በለስ (ሮማይስጥFicus) ቅጠሉ ሰፋፊ፣ ነጭ ፈሳሽ ያለው፣ ፍሬው የሚበላ የእፅዋት አስተኔ ነው። ፍሬውም ደግሞ በለስ ወይም ዕጸ በለስ ይባላል። በበለሱ ቤተሠብ ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ የዛፍ አይነቶች አሉ፤ ከነዚህም ውስጥ፦

  • ተራ በለስ F. carica ከጥንት ጀምሮ ስለ ፍሬው በእርሻ ወይም በጓሮ ተተክሏል። ፍሬውም ለጤንነት እጅግ መልካም ነው።
  • የቆላ በለስ F. palmata
  • ሾላ F sycomorus -
  • ዋርካ (ወይም ወርካ) F. vasta - በብዙ ቅርንጫፎች በጣም ትልቅ የሆነ የበለስ አይነት ነው። ፍሬው ከሾላ ፍሬ ያንሳል። ይህ ፍሬ ከበሰለና ከደረቀ በኋላ ይበላል።
  • የጎማ ዛፍ F. elastica
  • የቊልቋል በለስ (Opuntia) እውነተኛ በለስ ሳይሆን እንዲያውም ቊልቋል ነው። ሆኖም ፍሬውን ስለሚመስል ብዙ ጊዜ ይህም ተክል 'በለስ' ይባላል።

የበለስ 'ፍሬ' በዕውኑ ወደ ውስጥ ያበበ አበባ ነው። ይህ ክስተት ለሥነ ሕይወት ጥናት በጣም የሚያስገርም ድንቅ ነው። እነኚህ አበቦች የወንዴ ዘር የሚያገኙበት ዘዴ በልዩ ብናኝ አርካቢ ጥቃቅን ተርብ አማካኝነት ነው። ይህች የበለስ ተርብ ወደ ፍሬው ውስጥ ገብታ በመኖር እንቁላሏን በዚያ ትጥላለች። አለበለዚያ አብዛኞቹ በለስ አይነቶች ብናኝ ዘርን ሊያገኙ አይችሉም። ተርቢቱ ዕንቁላሏን ጥላ በበለሱ ውስጥ ከሞተች በኋላ፣ በፍሬው ያለው ኤንዛይም በድኑን ፈጽሞ ይበላል። የዛፉ ጾታ አንስት ከሆነ፣ የተርቢቱ እንቁላል አይፈለፈለም፣ ፍሬውም በሰው ይበላል። የዛፉ ጾታ ግን ፍናፍንት ሲሆን፣ ዕንቁላሎቿ ይፈለፈላሉ፤ ፍሬው ለፍየል ሊሰጥ ይችላል እንጂ በሰዎች አይበላም። ተርቦች ከፍናፍንት ዛፍ ተወልደው ሴት ተርቦቹ የሴት ዛፍ እንዲያገኙ ገበሬው የፍናፍንት ዛፍ ቅጠል ከአንስት ዛፍ ቅርንጫፍ ይሰቅላል። አንዳንድ የበለስ አይነት ያለ ተርብ ያፈራል፤ ነገር ግን የነዚህ ፍሬዎች መካን ይሆናሉ። ዳሩ ግን በለሶች በእፃዊ ተዋልዶ ለማብዛት በተለይ ስለሚመቹ፣ ይህ ዘዴ የተለመደና ፈጣን የመራቦ ዘዴ ነው።

እስልምና፣ በሕንዱ፣ በቡድሂስትና በጃይን እምነቶች፣ በለሶች የተቀደሱ ዛፎች ሆነው ይቆጠራሉ። በክርስትናም በአይሁድም በኩል በለስ ወይም ሾላ በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ለምሳሌ በአንዳንድ ሥፍራ በትንቢት፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ሰው ሁሉ በራሱ ወይንና በለስ ሥር እንደሚቀመጥ ይላል። በተጨማሪ በኦሪት ዘፍጥረት 3፡7 ዘንድ አዳምሕይዋን ከበለስ ቅጠል ልብስ ሠሩላቸው። ከዚህ የተነሣ በተለይ በተዋሕዶ ቤ.ክ. የበለስ ፍሬ ወይም እፀ-በለስ እግዚአብሔር እንዳትበሉት ብሎ ያዘዛቸው ፍሬ መሆኑን በመገመት ይታመናል። ሆኖም በሌላ አስተሳስብ የተከለከለው ፍሬ መታወቂያ ወይን ወይም ቱፋህ ነበር። መታወቂያው በመጽሐፉ እርግጠኛ ስላልሆነ፣ በእርግጥ በለስ ማለቱ ነበር ልንል አንችልም። በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ በለስ በክርስቶስ ምሳሌዎች ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል፤ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 11 መሠረት ኢየሱስም አንዲቱን በለስ ረግሞ ነበር።


የመደቦች ዝርዝር
Wikibar.png
አንብቡ፣ ጻፉ፣ ተሳተፉ።
enllaç=

ውክፔዲያ ዓለም-ዓቀፍ የዕውቀት ማከማቻ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ሁሉም ሰው በመዝገበ ዕውቀቱ እንዲሳተፍ ተፈቅዷል። አዳዲስ ተሳታፊዎች፣ የጀማሪዎች ማያያዣን በመጫን በፍጥነት ስለ ድረ-ገጹ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ወይንም ነባር ጽሑፍ ለማስተካከል ደፍሮ መሞከር ጥሩ ልምድ ነው። ከሌሎች ውክፔዲያዎች የተተረጎሙ ጽሑፎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ለዚህ ተግባር እነዚህን መዝገበ ቃላት ማማከር ይችላሉ ። የሚያቀርቡት ጽሑፍ ያልተሟላ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በተፈለገ ጊዜ ሊሻሻል ይችላልና።


ታሪክ በዛሬው ዕለት
enllaç=

ጥቅምት ፭

  • ፲፮፻፺፱ ዓ/ም - በዓፄ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥት ልዑል ሰገድ) ትዕዛዝ፣ ሸሽተው ጣና ሐይቅ ላይ በጨቅላ መንዞ ደሴት የነበሩትን አባታቸውን ዳግማዊ ኢያሱ አድያም ሰገድን ጳውሎስ እና ደርመን የተባሉ ነፍሰ ገዳዮች ሕይወታቸውን ካጠፉ በኋላ አስከሬናቸውን በእሳት አቃጠሉት። ከቃጠሎ የተረፈውን ካህናቱ በታንኳ ወስደው ምጽራሓ ደሴት ላይ ቀበሩት።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ ልጅ መቶ-ዓለቃ ልዑል መኮንን መኮንን ትምህርት ላይ ከነበሩበት ከአሜሪካ ወደአገራቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ደርግ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የሥራ ዕህቶች
enllaç=

ነጻ መጽሐፈ ዕውቀት የሆነው የውክፔዲያ አስተናጋጅ Wikimedia Foundation ነው።
ይህ ለትርፍ-ያልሆነ ድርጅት አያሌ ልዩ ልዩ ባለ ብዙ ቋንቋ እና የጋራ ጥቅም ሥራ እቅዶች ያካሂዳል፦

ለዕለቱ የተመረጠ ምስል
Wikibar.png

Rescue exercise RCA 2012.jpg )