ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
ወደ ውክፔዲያ እንኳን ደህና መጡ!

ይህ የአማርኛው ውክፔዲያ ጥር 18 ቀን 1996 ዓመተ ምሕረት
(27 January 2004 እ.ኤ.አ.) የተጀመረ ሲሆን አሁን 13,541 ጽሑፎችን አካቶ ይዟል።

አጠቃላይ የውክፔዲያ አጠቃቀም መልመጃ ለጀማሪዎች እሚለው ማያያዣ ላይ ይገኛል።

መግቢያ
enllaç=
      ወደ ውክፔዲያ እንኳን ደህና መጡ! ውክፔዲያ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሁሉም ዓይነት ዕውቀት እየተመዘገበ እና እየተነበበ ያለበት ዓለም ዓቀፍ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ማንም ሰው በመዝገበ ዕውቀቱ ለመሳተፍ ይቻለዋል/ይቻላታል። አዲስ ተሳታፊዎች፣ ለጀማሪዎች የሚለውን ማያያዣ በመጫን ብዙ መረጃዎች ያገኛሉ ።
    

አዲስ ጽሑፍ ለመጀመር ወይንም ነባር ጽሑፍ ለማስተካከል ደፍሮ መሞከር ጥሩ ልምድ ነው። የሚቀርበው ጽሑፍ ያልተሟላ፣ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በሌላ ጊዜ ሊሻሻል እና ሊጠናቀቅ ይቻላል። እርስዎ ጽሑፍ ለማቅረብ ከፍለጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።

የመደቦች፡ዝርዝር።
Wikibar.png
የዕለቱ፡ምርጥ፡ጽሑፍ።
enllaç=

የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች


Visa requirements for Ethiopian citizens.png


የቪዛ መስፈርቶች ለኢትዮጵያ ዜጎች በየአገሩ ይለያያሉ። አንድ አንድ አገሮችን (ካርታው ላይ በግራጫ ያሉ) ፣ ኢትዮጵያውያን ሊጎበኙ ቢፈልጉ መግቢያ ፈቃድ ማሕተም ያስፈልጋቸዋል። ሆኖም አንዳንድ አገራት (ለምሳሌ፦ ዶመኒካ) ያለ ምንም ቪዛ ሂደት ኢትዮጵያውያን ለተወሰነ ጊዜ እንዲጎብኙ ይፈቅዳሉ፣ እንዲሁም አንዳንድ አገራት (ለምሳሌ፦ ኒካራጓ) ኢትዮጵያውያን እዚያ በደረሱ ጊዜ የመግቢያ ፈቃድ ይሰጣቸዋል። የበለጠ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ . . .
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።
enllaç=

ግንቦት ፳፬

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባአስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ።
  • ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከዘጠኝ ወራት በኋላ ነጻነቷን የተቀዳጀችው ኬንያ፣ በዛሬው ዕለት እራሷን የማስተዳደር መብት ተፈቀደላት። ይሄንን ዕለት በየዓመቱ “የማንዳራካ ቀን” በሚል ስያሜ ኬንያ ታከብረዋለች።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (አሁን ዚምባብዌ) በ፺ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች የሚመራ መንግሥት ሥልጣንን ጨበጠ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - ‘ሲ. ኤን. ኤን.’ (CNN) የተባለው የዜና ማሠራጫ ድርጅት ሥራውን ጀመረ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - የኔፓል አልጋ ወራሽ ልዑል ዲፔንድራ አባታቸውን ንጉሥ ቢሬንድራን፤ እናታቸውን ንግሥት አይስዋርያን እና ሌሎችንም ንጉሣዊ ቤተ ሰባቸውን ረሽነው ከገደሉ በኋላ እራሳቸውንም በጥይት አጠፉ።
የዕለቱ፡ምርጥ፡ ምሥል።
enllaç=
Allianz arena daylight Richard Bartz.jpg
የሥራ፡እህቶች።
Wikibar.png