ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
ለዕለቱ የተመረጠ ጽሑፍ
enllaç=

ቢግ ማክሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።

ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።


የመደቦች ዝርዝር
አንብቡ፣ ጻፉ፣ ተሳተፉ።
enllaç=

ውክፔዲያ ዓለም-ዓቀፍ የዕውቀት ማከማቻ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ሁሉም ሰው በመዝገበ ዕውቀቱ እንዲሳተፍ ተፈቅዷል። አዳዲስ ተሳታፊዎች፣ የጀማሪዎች ማያያዣን በመጫን በፍጥነት ስለ ድረ-ገጹ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ወይንም ነባር ጽሑፍ ለማስተካከል ደፍሮ መሞከር ጥሩ ልምድ ነው። ከሌሎች ውክፔዲያዎች የተተረጎሙ ጽሑፎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ለዚህ ተግባር እነዚህን መዝገበ ቃላት ማማከር ይችላሉ ። የሚያቀርቡት ጽሑፍ ያልተሟላ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በተፈለገ ጊዜ ሊሻሻል ይችላልና።


ታሪክ በዛሬው ዕለት
enllaç=

ታኅሣሥ ፲፪

  • ፲፰፻፲ ዓ/ም - በዘመነ መሳፍንት ፮ ጊዜ ከንጉሥነት ሥልጣናቸው የተሻሩት እና የነገሡት ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ በዚህ ዕለት በትግሬው መሥፍን በራስ ወልደ ሥላሴ ዘመን አርፈው፣ አክሱም ጨለቆት ሥላሴ ተቀበሩ።
  • ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የጎጃሙ ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት አማቻቸው የነበሩትን ደጃዝማች አበራ ካሣን እና ወንድማቸውን ደጃዝማች አስፋ ወሰን ካሣን ‘አይዟችሁ አትነኩም’ ብለው አታለው ካስገቡ በኋላ አሳልፈው ለፋሺስት ኢጣልያ ኃይሎች አስረከቧቸው። የጣልያኖቹም ጄኔራል ትራኪያ ወንድማማቾቹን ፍቼ ላይ በዚህ ዕለት አስረሽኖ አንገታቸውን አስቆርጦ ገደላቸው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት "የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብአዊነት"ን (የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም) በይፋ ካወጀ በኋላ፣ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው "ብሔራዊ የዕድገት በኅብረት የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ" የተሰኘ ፷ ሺ የሁለተኛ ደረጃ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን በመላ አገሪቱ አሰማራ። የጊዘውም መፈክር ፣"በዕድገት በኅብረት - እንዝመት፣ ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት" የሚል ነበር
የሥራ ዕህቶች
enllaç=

ነጻ መጽሐፈ ዕውቀት የሆነው የውክፔዲያ አስተናጋጅ Wikimedia Foundation ነው።
ይህ ለትርፍ-ያልሆነ ድርጅት አያሌ ልዩ ልዩ ባለ ብዙ ቋንቋ እና የጋራ ጥቅም ሥራ እቅዶች ያካሂዳል፦

ለዕለቱ የተመረጠ ምስል