አንብቡ፣ ጻፉ፣ ተሳተፉ።
|
|
ውክፔዲያ ዓለም-ዓቀፍ የዕውቀት ማከማቻ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ሁሉም ሰው በመዝገበ ዕውቀቱ እንዲሳተፍ ተፈቅዷል። አዳዲስ ተሳታፊዎች፣ የጀማሪዎች ማያያዣን በመጫን በፍጥነት ስለ ድረ-ገጹ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ወይንም ነባር ጽሑፍ ለማስተካከል ደፍሮ መሞከር ጥሩ ልምድ ነው። ከሌሎች ውክፔዲያዎች የተተረጎሙ ጽሑፎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ለዚህ ተግባር እነዚህን መዝገበ ቃላት ማማከር ይችላሉ ። የሚያቀርቡት ጽሑፍ ያልተሟላ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በተፈለገ ጊዜ ሊሻሻል ይችላልና።
|
|
|
|
ታሪክ በዛሬው ዕለት
|
|
- ፲፮፻፲፮ ዓ/ም - ዠሮም ሎቦ እና ሌሎችም የብርቱጋል ሚሲዮናዊያን ከደንቀዝ በተነሱ በስድስተኛው ቀን በቀድሞ ስሟ “ማይ ጓጓ” (የውሐ ጩኸት) ከምትባለው በኋላ ብርቱጋሎች ለአቡነፍሬምናጦስ ማስታወሻ ከአድዋ አጠገብ ‘ፍሪሞና’ ብለው ከሰየሟት ሥፍራ ደረሱ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋጋው በ፳፮ ሚሊዮን ፮፻፴፭ ሺ ፫፻፸፰ የእንግሊዝ ፓውንድ (£26,635,378.25) የተገመተ እና በጠቅላላው ሚዛኑ ፲፬ ሺ ፻፴፬ ኪሎ ከ ፭፻፸፮ ግራም ያልተጣራ ወርቅ በድብቅ ጭኖ በአቴና በኩል ሎንዶን ገብቷል።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -የኤርትራ ነፃነት ግንባር መጋቢት ፲፯ ቀን ኤርትራ ውስጥ ከጠለፋቸው አምስት የ’ቴናኮ’ (Tennaco) ነዳጅ ምርመራ ባልደረቦች መኻል አንድ ካናዳዊ የሄሊኮፕተር አብራሪ በዚህ ዕለት ለቀቁ።
|
|
|