የእኛን አገልግሎቶች በሚጠቀሙበት ጊዜ፣ ለእርስዎ መረጃ እኛን እምነት ይጥሉብናል። ምን እንደምናደርግበት ለእርስዎ በመንገር መጀመር እንፈልጋለን፦
ውሂብ እንደ ፍለጋ፣ Gmail እና ካርታዎች ያሉ አገልግሎታችንን እንድናቀርባቸው ያስችለናል።
የእኛን አገልግሎቶች ለእያንዳንዱ ሰው ነጻ ማድረግ እንድንችል ውሂብ በተጨማሪ ተዛማጅነት ያላቸውን ማስታወቂያዎች እንድናሳይ ያግዘናል።
የእርስዎን የግል መረጃ እንደማንሸጥ ይወቁ።
እናም እኛ የምንሰበስበውን እና የምንጠቀምበትን መረጃ ዓይነቶች መቆጣጠር ይችላሉ።
በመጨረሻ የእርስዎን እና የመረጃዎን ደህንነት ለመጠበቅ ከዚህ በላይ የሚሰራ ማንም የለም።
ስለግላዊነት እና ደህንነት በተለምዶ ለምንሰማቸው ጥያቄዎች መልሶችን እዚህ ላይ ማግኘት ይችላሉ፦።
የምንሰበስበው ውሂብ ዋንኛ ዓይነቶች እንደ የእርስዎ መሰረታዊ የመለያ ዝርዝሮች የመሳሰሉ እና እርስዎ የፈጠሩዋቸውን ነገሮች የመሳሳሉ የእኛን አገልግሎት በመጠቀም የወሰዱዋቸው እርምጃዎች ላይ የተመረኮዙ ናቸው።
አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ – ለምሳሌ፣ Google ላይ ፍለጋ ሲያከናውኑ፣ Google ካርታዎች ላይ አቅጣጫዎችን ሲያገኙ፣ ወይም YouTube ላይ ቪዲዮ ሲመለከቱ – አገልግሎቶቻችን ለእርስዎ በተሻለ ሁኔታ ለእርስዎ እንዲሰሩ መረጃ እንሰበስባለን። ለአንድ Google መለያ ሲመዘገቡ እንደ የእርስዎ ስም፣ ኢሜይል እና የይለፍ ቃል ያሉ ለእኛ የሚሰጡን የመለያ መረጃዎችን እናስቀምጣለን። እና አገልግሎቶቻችንን በመጠቀም የሚፈጥሯቸውን ነገሮች አከማችተን እንጠብቃቸዋለን፣ ስለዚህ ሁልጊዜ የእርስዎ ኢሜይሎች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና ሰነዶች ሲያስፈልገዎት ያገኟቸዋል።
የምንሰበስበው እና የምንጠቀመው የውሂብ አይነቶችን ለመቆጣጠር መሣሪያዎችን እንሰጠዎታለን።
ቀዳሚው እና ዋና ነገሩ ውሂብ የምንጠቀመው አገልግሎታችን ይበልጥ ፈጣን፣ ዘመናዊ እና ለእርስዎ ጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ነው፣ ለምሳሌ የተሻለ የፍለጋ ውጤቶችን እና ጊዜያቸውን የጠበቁ የትራፊክ ዝማኔዎች ማቅረብ። ውሂብ እንዲሁም እርስዎን ከተንኮል-አዘል ዌር፣ ማስገር እና ሌላ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመጠበቅ ስርዓተ ጥለቶችን ለመጠበቅም ያግዛል። ለምሳሌ፣ አደገኛ ድር ጣቢያዎችን ለመጎብኘት ሲሞክሩ እናስጠነቅቀዎታለን። እንዲሁም ተገቢ እና ጠቃሚ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማሳየት እና አገልግሎቶቻችን ለሁሉም ሰው ነጻ ለማድረግ ውሂብ እንጠቀማለን።
አይ። የግል መረጃዎን አንሸጥም።
የምናሳየዎት ማስታወቂያዎች ይበልጥ ተገቢ እና ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደ ያከናወኗቸው ፍለጋዎች እና የእርስዎ አካባቢ ያለ የተወሰነ መረጃ እንጠቀማለን። እንደ ፍለጋ፣ Gmail እና ካርታዎች ያሉ አገልግሎቶቻችን ለሁሉም ሰው ነጻ እንድናደርግ የሚያስችሉን ማስታወቂያዎች ናቸው። እርስዎ ካልጠየቁን በስተቀር ይህን መረጃ እርስዎ ለመለየት በሚያስችል መልኩ ለማስታወቂያ ሰሪዎች አናሳይም። በማስታወቂያዎች ቅንብሮች መሣሪያችን አማካኝነት በፍላጎቶችዎ እና ባከናወኗቸው ፍለጋዎች ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ።
Google እንዴት ለእርስዎ እንደሚሰራ እንዲቆጣጠሩ የሚያግዘዎት ለመጠቀም ቀላል የሆኑ መሣሪያዎች አሉን።
በየእኔ መለያ ውስጥ የእርስዎን ግላዊነት እና መረጃ ሁሉ በአንድ ቦታ የሚያቀናብሩባቸውን መሣሪያዎች ማግኘት ይችላሉ።
በየእንቅስቃሴ ቁጥጥሮች ውስጥ ባሉ የውሂብ መቆጣጠሪያዎች አማካኝነት የእርስዎን የፍለጋ፣ YouTube እና የአካባቢ እንቅስቃሴ ጨምሮ የምንሰበስበው የውሂብ አይነቶችን ማቀናበር ይችላሉ።
በእኛ የማስታወቂያዎች ቅንብሮች መሣሪያ አማካኝነት በፍላጎቶችዎ እና ባከናወኗቸው ፍለጋዎች ላይ የተመሠረቱ ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር ይችላሉ።
የመረጃዎ ደህንነት ካልተጠበቀ በግል የተያዘ አይደለም። ለዚህ ነው የGoogle አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ በጣም ከተራቀቁ የዓለም የደህንነት መሠረተ ልማቶች ውስጥ በአንዱ የሚጠበቁት።
ከ1 ቢሊዮን በላይ ሰዎችን የሚጠብቀው የGoogle የደህንነት አሰሳ ቴክኖሎጂ ተንኮል-አዘል ዌር ወይም የማስገር ሙከራ ያለው ጣቢያ ለመጎብኘት ሲሞክሩ ያስጠነቅቀዎታል።
ምስጠራ የእርስዎ መረጃ በመሣሪያዎ እና በGoogle መካከል ሲመላለስ ደህንነቱ በይበልጥ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል።
የGmail ደህንነት ከሌላ ማንኛውም የኢሜይል አገልግሎት በተሻለ መልኩ እርስዎን ከአይፈለጌ መልዕክት፣ ማስገር እና ተንኮል-አዘል ዌር ይጠብቀዎታል።
ሁሉም ምርቶቻችን በላቀ የመስመር ላይ ደህንነት የተገነቡ ናቸው። መረጃዎን በጥንቃቄ ለመያዝ ማድረግ የሚችሏቸውን ሶስት ቀላል ግን አስፈላጊ ነገሮች እነሆ።
የGoogle መለያዎን ደህንነት ለመጠበቅ የደህንነት ፍተሻውን በመደበኝነት ይጠቀሙ። ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚወስደው።
ጠንካራ የይለፍ ቃል ይውሰዱ፣ ከዚያ ከGoogle መለያዎ ውጪ በጭራሽ ለሌላ ነገር አይጠቀሙበት።
መለያዎ ላይ የመልሶ ማግኛ ስልክ ቁጥር ያክሉ፣ በዚህም ቢቆለፍብዎ ወይም የሆነ ሰው ለመግባት እየሞከረ ነው ብለን ካሰብን ማንነትዎን ማረጋገጥ እንችላለን።
የእርስዎን ግላዊነት እና ደህንነት የሚያቀናብሩባቸው መሣሪያዎችን ለማግኘት ወደ የእኔ መለያ ይሂዱ።