ስታትስቲክስ

ተመልካችነት

  • በየወሩ ከ1 ቢሊዮን በላይ ልዩ ተጠቃሚዎች YouTubeን ይጎበኙታል
  • በእያንዳንዱ ወር ከ6 ቢሊዮን ሰዓታት በላይ የሚሆን ቪዲዮ በYouTube ላይ ይታያል—ይህ ማለት በምድር ላይ ለሚኖር እያንዳንዱ ሰው አንድ ሰዓት ያህል ማለት ነው
  • በየደቂቃው የ72 ሰዓቶች ቪዲዮዎች ወደ YouTube ይሰቀላሉ
  • 80% የሚሆነው የYouTube ትራፊክ የሚመጣው ከአሜሪካ ውጪ ነው
  • YouTube በ61 አገሮችና በ61 ቋንቋዎች ተተርጉሟል
  • ኒልሰን በሚለው መሠረት YouTube በአሜሪካ ውስጥ ከማንኛውም የኬብል ቴሌቪዥን በላይ ዕድሜያቸው 18-34 የሆኑ አዋቂዎችን ይደርሳል።
  • በእያንዳንዱ ቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዝገባዎች ይደረጋሉ። በየቀኑ የሚመዘገቡት ሰዎች ቁጥር ከአለፈው አመት ጀምሮ በ3 እጥፍ ያደገ ሲሆን የቀን ምዝገባዎች ቁጥር ደግሞ ከአለፈው አመት ጀምሮ በ4 እጥፍ አድጓል

YouTube አጋር መርሀግብር

  • በ 2007 የተፈጠረ፣ ከ30 ሃገራት በላይ በዓለም ዙሪያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የፈጠራ ባለቤቶች በYouTube ቪዲዮዎቻቸው አማካይነት ገንዘብ ያገኛሉ።
  • በሺዎች የሚቆጠሩ ሰርጦች በዓመት ባለስድስት አኃዝ ገቢ ያገኛሉ

ገቢ መፍጠር

  • በሺዎች የሚቆጠሩ አስተቃዋቂዎች TrueView ውስጠ-ዥረትን እየተጠቀሙ ናቸው፣ እና 75% የሚሆነው የውስጠ-ዥረት ማስታወቂያዎቻችን አሁን ሊዘለሉ የሚችሉ ናቸው
  • የGoogle ማስታወቂያ መድረኮችን የሚጠቀሙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የማስታወቂያ ሰሪዎች አሉን፣ አብዛኛዎቹ ደግሞ አነስተኛ ንግዶች ናቸው

ተንቀሳቃሽ ስልክ እና መሣሪያዎች

  • ተንቀሳቃሽ ስልክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን 40% ያህል የYouTube የእይታ ጊዜ ይይዛል
  • YouTube በመቶ ሚሊዮኖች በሚቆጠሩ መሣሪያዎች ላይ ይገኛል

የይዘት መታወቂያ

  • Content ID በየቀኑ ከ400 ዓመት በላይ የሚሆኑ ቪዲዮዎች ይቃኛል
  • እያንዳንዱን ዋና ዋና የአሜሪካ የአውታረመረብ ማሰራጫዎችን ጨምሮ፣ የፊልም ስቱዲዮዎች እና የምዝገባ ድርጅቶች ጨምሮ ከ5000 በላይ ባልደረባዎች የይዘት መለያ ይጠቀማሉ
  • በይዘት መለያ ውሂብ ጎታችን ውስጥ ከ25 ሚሊዮን በላይ የማጣቀሻ ፋይሎች አሉን፤ በዓለማችን ላይ እጅግ ሁሉን አቀፍ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው
  • የይዘት መታወቂያ በመቶዎች ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለአጋሮች አመንጭቷል