ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ለዕለቱ የተመረጠ ጽሑፍ
enllaç=

ብርሃን

Livarnolux LED-Fiberglasleuchte.JPG


ብርሃን ማስተላለፊያ ቀጭን ትቦዎች
ብርሃን አካላትዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ የተፈጥሮ ሞገድ ነው። የብርሃን ሞገድ ከኤሌክትሪክ እና ከመግነጢስ የተሰራ ስለሆነ ሞገዱ የ ኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ይባላል። ይሁንና፣ የኤሌክትሮመግነጢስ ጨረራ ብርሃንን ብቻ ሳይሆን የብርሃንን ታናናሽና ታላላቅ ወንድሞች ሳይቀር ያቅፋል። ከብርሃን ታናናሽ ወንድሞች፣ ለራዲዮና እና ቴሌቪዥን ስርጭት የሚያገለግለው የራዲዮ ሞገድራዳር እና ሙቀት አስተላላፊው ታህታይ ቀይ ይገኙበታል። ታላላቆቹ ደግሞ ላዕላይ ወይን ጠጅኤክስ ሬይጋማ ጨረር ይባላሉ። እነዚህ የብርሃን ወንድሞች በመሰረታዊ ተፈጥሯቸው ከብርሃን ጋር አንድ ቢሆኑም ፣ የሰው ዓይን ሊያያቸው ስለማይችል ብርሃን አይባሉም። አንድ አንድ እንስሳት በአንጻሩ እነዚህን ሞገዶች መመልከት ይችላላሉ። ለምሳሌ ታህታይ ቀይ የሚባለው የብርሃን ታናሽ ወንድም፣ ለሰዎች እንደ ሙቀት ሆኖ ይሰማል። ለምሳሌ የፀሐይ መሞቅ ከምትተፋው የታህታይ ቀይ ጨረራ ይመነጫል። በበረሃ የሚንከላዎሱ እባቦች ይህን ሞገድ በአይናቸው መመልከት ስለሚችሉ፣ ሙቀት ያለውን ማንኛውንም ነገር በጭለማ ሳይቀር ማየት ይችላሉ። ንቦች በተራቸው፣ የሰው ልጅ እማያየውን ላዕላልይ ወይን ጠጅ ሞገድ በዓይናቸው ማየት ስለሚችሉ፣ አበቦች ለንቦች ከሰው ልጅ የተለየ መልክና መልዕክት ያስተላልፋሉ።


የመደቦች ዝርዝር
Wikibar.png
አንብቡ፣ ጻፉ፣ ተሳተፉ።
enllaç=

ውክፔዲያ ዓለም-ዓቀፍ የዕውቀት ማከማቻ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ሁሉም ሰው በመዝገበ ዕውቀቱ እንዲሳተፍ ተፈቅዷል። አዳዲስ ተሳታፊዎች፣ የጀማሪዎች ማያያዣን በመጫን በፍጥነት ስለ ድረ-ገጹ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

አዲስ ጽሑፍ ለመጻፍ ወይንም ነባር ጽሑፍ ለማስተካከል ደፍሮ መሞከር ጥሩ ልምድ ነው። ከሌሎች ውክፔዲያዎች የተተረጎሙ ጽሑፎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ። ለዚህ ተግባር እነዚህን መዝገበ ቃላት ማማከር ይችላሉ ። የሚያቀርቡት ጽሑፍ ያልተሟላ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በተፈለገ ጊዜ ሊሻሻል ይችላልና።


ታሪክ በዛሬው ዕለት
enllaç=

መጋቢት ፲፱

  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የንግድ እና ኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የቱርክ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ‘አንጎራ’ ስሟ ተለውጦ አንካራ ስትባል፤ የአገሪቱ አንደኛ ከተማ እና በሮማይስጡ ቄሳር ቁስጥንጢኖስ የተመሠረተችው ቁስጥንጢንያ ወይም ኮንስታንቲኖፕል (Constantinople) ስሟን ቀይራ ኢስታንቡል ተባለች።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ ከተሰነዘሩት ዐበያት ሕዝባዊ እሮሮዎች አንዱ በመሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ግፈኝነት እና ሙስና ስለነበር ይሄንኑ ጉዳይ እንዲያጠና የተመሠረተው ኮሚሲዮን አባላት ተሠየሙ።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ፤ በጆሃንስበርግ ከተማ፣ በዙሉዎችና ‘የአፍሪቃ ብሔራዊ ሸንጎ’ (African National Congress) ደጋፊዎች መኻል በተከሰተው ሽብር አሥራ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የሥራ ዕህቶች
enllaç=

ነጻ መጽሐፈ ዕውቀት የሆነው የውክፔዲያ አስተናጋጅ Wikimedia Foundation ነው።
ይህ ለትርፍ-ያልሆነ ድርጅት አያሌ ልዩ ልዩ ባለ ብዙ ቋንቋ እና የጋራ ጥቅም ሥራ እቅዶች ያካሂዳል፦

ለዕለቱ የተመረጠ ምስል
Wikibar.png

Black-headed weaver (Ploceus cucullatus bohndorffi) male nest building.jpg