ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ግለሰቦች በስልኮቻቸው አማካኝነት ምን እንደሚያወሩ ተደብቆ ለመስማት እና መረጃን ለመስብሰብ የሚያስችል አዲስ ክህሎትን በስልጣን ላይ ለተቀመጡ አካላት ሰጥቷል። ይህ የEFF ራስን ከስለላ ጥቃት የመከላከያ መመሪያ ደህንነቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ራስዎን እና ወዳጅዎትን ከጆሮ ጠቢዎች እንዲከላከሉ እና ጠንቃቃ የኾነ ልምምድ እንዲያዳብሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ስለተለያዩ መርጃ መሳሪዎች ወይም ጉዳዮች ለማወቅ ከመረጃ ጠቋሚ መጣጥፎች ይምረጡ ወይም ስለተለያዩ አዳዲስ ክህሎት የድጋፍ ቅኝት ለማድረግ ከፈለጉ ከዲጂታል ዝርዝር መካከል አንዱን ይመልከቱ።

አጭር መግለጫ

የዲጂታል ስለላ ምንድን ነው እንዴትስ ይከላከሉታል፤ መሠረታዊ ነጥቦች።

 
ቱቶሪያሎች

ለአጠቃቀም ቀላል የኾኑ ሶፍርዌሮችን እና መሳሪያዎችን እንዲጭኑ እና እንዲጠቀሙ የሚረዳ ቅደም ተከተላዊ መመሪያ።

 
ገለፃዎች

ለተወሰኑ ሁኔታዎች የሚጠቅም ጥልቀት ያለው መመሪያ።

 
JavaScript license information