ፕሬዝደንት መሐመድ ከሪያድ ጎን አለመቆማቸዉ የተረጋጋ መንግሥታቸዉን አደጋ ላይ እንዳይጥለዉ ስጋት አለ። ፕሬዝደንት መሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ፤ በአረብ ሐገራት ዉዝግብ መንግስታቸዉ ገለልተኛ አቋም እንዲይዝ ማድረጋቸዉ ብዙዎችን አስገርሟል። አስተዳደራቸዉም ወንድማማቾቹ ሃገራት ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቧል። ይህም በአካባቢዉ ፤ በተለይም በሶማሊያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ላላቸዉ ለሳዑዲ እና ለተባበረዉ አረብ ኤሜሬቶች አስደንጋጭ ሆኗል። ሳዑዲ አረቢያ የሶማሊያ ዋነኛ የንግድ አጋር ናት።ፕሬዝደንት ፎርማጆ በየጊዜዉ ለሶማሊያ ጠቀም ያለ ገንዘብ የምትለግሰዉን እና በተመረጡ ማግሥት