ካለፈው ዓመት የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት አንስቶ ነበር ፣ የባልካን የጉዞ መስመርን ተከትለው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሶርያውያን አፍጋናውያን እና ኢራቆች የሚያመዝኑባቸው ስደተኞች ጀርመን መግባት የጀመሩት ።ይህ የሆነውም ጀርመን ሳይታሰብ ድንበሯን ክፍት ካደረገች በኋላ ነው ። በዚሁ መሠረት ከጎርጎሮሳዊው መስከረም 2015 እስከ ሐምሌ 2016 ፣ 900,623 ስደተኞች ጀርመን መግባታቸው ተመዝግቧል ። ያኔ ጀርመን በሯን ለስደተኞች ክፍት ማድረጓ በተቀረው ዓለም ሲደነቅ ከሃገር ውስጥ እርምጃውን የደገፉ እንደነበሩ ሁሉ የተቃወሙም አልጠፉም ። በወቅቱ ስጋታቸውን ለሚገልጹ ወገኖች መራሂተ መንግሥት