የተዋቡ አዉራ ጎዳናዎች፣ ሰማይ ጠቀስ እና አንጸባራቂ ሕንፃዎች ያሏት ኩየት ላለፉት አስርት ዓመታት ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ሠራተኞችን የምትስብ ማግኔት ሆና ቆይታለች። በንጉሥ የምትተዳደረዋ ሀገር ሥራም ሆነ አዲስ የመኖሪያ ሥፍራ በሚፈልጉ ተመራጭ ነበረች። ሆኖም ይህ ገፅታዋ ከደበዘዘ ሰነበተ። አሁን ኩየት የተወሰኑ ሰዎችን ነዉ ወደግዛቷ እንዲገቡ የምትፈቅደዉ፤ ስደተኛ ግን መሆን የለበትም። ጦርነት የሚሸሸዉ የሶርያ ስደተኛ ግን የ29 ዓመቱ የኩየት ዜጋ አብደላ እንደሚለዉ ምንም ቢሆን