በኤኳቶርያል ጊኒ ካሉት ትልቆቹ የነዳጅ ዘይት ንጣፎች መካከል አንዱ ፑንቶ ኦይሮፓ ሲሆን፣ በዚሁ ከመሀል ሀገር 200 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የቢዮኮ ደሴት ባለው ስፍራ የነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ማውጣት ሂደት ተጧጡፎ ይካሄዳል፤ በዚሁ ሂደት ውስጥም በየሌሊቱ የእሳት ነበልባል ከሩቁ ይታያል። የተፈጥሮ ሀብቷ ነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ለኤኳቶርያል ጊኒ ብልፅግና ያስገኘላት ሲሆን፣ በዓለም ባንክ ዘገባ መሰረት፣ በሀገሪቱ አማካዩ የነፍስ ወከፍ ገቢ 23,000 ዩኤስ ዶላር ነው። ይህ ታንዛንያ ወይም ሴኔጋልን ከመሳሳሉ አፍሪቃውያት ወይም ሀንጋሪን ከመሳሰሉ አውሮጳውያት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር በአስር እጥፍ