ሩሲያ በዓለም ፖለቲካ ያላትን ተደማጭነት በአዲስ መልክ ለመገንባት ጥረት ጀምራለች። የሶርያ ጦርነትን እጣ ፈንታ የምትወስነው ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ ልዕለ ኃያልነትን ለብቻዋ የተቆጣጠረች የምትመስለው ዩኤስ አሜሪካ አይደለችም የሚል መልዕክት ማስተላለፍ የፈለገችም ይመስላል። ለማንኛውም ሩሲያ በሶርያ እና ኢራቅ «እስላማዊ መንግስት መስርቻለሁ» በሚለው ጽንፈኛ የ«አይ.ኤስ.»ቡድን ላይ ከ12 ቀናት በፊት የአየር ጥቃት የጀመረችው በምዕራባዊ ሶርያ ነበር። ጥቃቱ ጥቂት ቆየት ብሎ ከካስፒያን ባህር ላይ ካሉ የጦር መርከቦች የሚምዘገዘጉ ክሩዝ ሚሳዔሎችንም ጨምሮዋል። የሩሲያ ጦር አዛዦች ጥቃቱን