ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ወደ ውክፔዲያ እንኳን ደህና መጡ!

ይህ የአማርኛው ውክፔዲያ ጥር 18 ቀን 1996 ዓመተ ምሕረት
(27 January 2004 እ.ኤ.አ.) የተጀመረ ሲሆን አሁን 13,061 ጽሑፎችን አካቶ ይዟል።

አጠቃላይ የውክፔዲያ አጠቃቀም መልመጃ ለጀማሪዎች እሚለው ማያያዣ ላይ ይገኛል።

መግቢያ፡ሐተታ።
enllaç=
      ወደ ውክፔዲያ እንኳን ደህና መጡ! ውክፔዲያ የብዙ አገር ሰዎች ተሰባስበው በልዩ ልዩ ቋንቋ'ዎች የዓለምን ዕውቀት እየመዘገቡ እና እያነበቡ ያሉበት ታዋቂ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ማንም ሰው ይህን መዝገበ ዕውቀት ሊያሻሽል ይችላል። እርስዎ ለውክፔዲያ አዲስ ከሆኑ ለጀማሪዎች የሚለውን ማያያዣ ቢጫኑ የበለጠ መረጃ ያገኛሉ ።

እዚህ ውክፔዲያ ላይ ጽሑፍ ለማቅረብ፡

  • መድፈር -- አዲስ ጽሑፍ ለመጀመር ወይንም ያለውን ጽሑፍ ለማስተካከል መድፈር ጥሩ ነው። የሚቀርበው ጽሑፍ ያልተሟላ፣ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ መጨነቅ አያስፈልግም። ጅምር ጽሑፍ በሌላ ጊዜ ሊስተካክል፣ ሊሻሻል እና ሊጠናቀቅ ይችላል።
  • መማር እና ማስተማር -- በማንኛውም የዕውቀት ዘርፍ ለመሳተፍ ይቻላል። ተማሪዎች በጥናታቸው ጊዜ እሚያጠኑትን ትምህርት ተርጉመው በጥቂቱ ቢጽፉ ለጥናታቸው ይረዳቸዋል።
  • መተርጎም -- ጽሑፍ ለማቅረብ የግዴታ ከባዶ መነሳት አያስፈልግም። ከእንግሊዝኛው ውክፔዲያ ወይም ከሌላ ቋንቋ ውክፔዲያም ትርጉም ጽሑፍ ማቅረብ የጽሁፍ ስራን ያቀለዋል።
የመደቦች፡ዝርዝር።
Wikibar.png
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስል።
enllaç=

Sternbergia clusiana 1.JPG Sternbergia clusiana (Amaryllidaceae) blooming in the Golan Heights, November 8, 2006.

ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።
enllaç=

መስከረም ፳፱

የዕለቱ፡ምርጥ፡ ጽሑፍ።
enllaç=

መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ


Holy Trinity Cathedral Addis Abeba.jpg

የመንበር ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልአዲስ አበባ ከተማ፣ አራት ኪሎ ሰፈር የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው። የቅድስት ስላሴ የመሠረት ድንጋይ ታኅሣሥ ፲፭ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲያስቀምጡ የእስክንድርያ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ እና የሀገር ጳጳሳትም በተገኙበት ልዩ ጸሎት እና ቡራኬ ተሠጥቶ ተመረቀ።

ቤተክርስቲያኑ በመጀመሪያ ዙር ልዩ መልክ ባለው እቅድ ተገንብቶ በሮችን መገጣጠምና ጌጣ ጌጥ ነገሮችን ማስገባት ሲቀር በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ለመውረር ስለተነሳ ሥራው መቆም ግድ ሆነበት። የፋሺስት ኢጣልያም ጠቅላላ ኃሣብ የኢትዮጵያን ሙሉ ክብር ፈጽሞ ለመግፈፍ እና የእራሱን አሻራ ለማላከክ ስለነበር፣ የዚህን ካቴድራል የአሠራር ጥራት እና የቦታውንም አቀማመጥ ምቹነት በመገንዘብ የካቶሊክ ካቴድራል ለማድረግ ወሰነ። ሆኖም በግድ እና በግፍ ወሰደው ላመባል ግምቱን ሰጥቶ መውሰድን መርጦ የጊዜውን የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች በማስፈራራት ግምት ከፍዬ ልውሰደው ሲል ጠየቃቸው። ያገኘው መልስ ግን «ዛሬ መብቱ ያንተ ነው። በግድ ለመውሰድ ትችላለህ፤ ግን በፈቃዳችን አናደርገውም» የሚል ቆራጥ መልስ በመሆኑ፣ እጠላት እጅ ሳይገባ ቀረ።

፲፱፻፴፫ ዓ/ም በተገኘው ድል ንጉሠ ነገሥቱ ሲመለሱ፣ የሕንፃው ሥራ እንደገና ተጀምሮ በቅልጥፍና ተሠርቶ ካለቀ በኋላ “መንበረ ፀባዖት” ተብሎ በቅድስት ሥላሴ ስም ተሰይሞ ጥር ፯ ቀን ፲፱፻፴፮ ዓ/ም፤ መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ሊቃውንት፣ የሴት ወይዛዝር፣ የጦር ሠራዊት በተገኙበት ተመረቀ። ካቴድራሉ መታሰቢያነቱም በ፭ቱ የጠላት ወረራ ዓመታት ለተዋጉት አርበኞች ሆነ። ቅዳሴ ቤቱ ከተባረከ በኋላ በባህር የተጣሉትን፤ በገደል የወደቁትን እና በማይታወቅ ቦት የረገፉትን አርበኞች ዐጽም ተሰብስቦ በዚሁ ዕለት በልዩ የጸሎት ሥነ ሥርዓትና በታላቅ የሰልፍ አጀብ ተቀበረ።
የሥራ፡እህቶች።
Wikibar.png