ዋና ገጽ

ከWiktionary
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

free dictionary

free online Amharic dictionary

free multilingual dictionary

free translation dictionary

free Amharic dictionary

Amharic pronunciation dictionary

wiki dictionary

Amharic wiki dictionary

multilingual dictionary and thesaurus

free online multilingual dictionary

GFDL dictionary

Flag of Ethiopia (1991-1996).svg
አንኳን ወደ ዊኪ-መዝገበ-ቃላት በደህና መጡ!

ረቡዕ, 1. ሜይ 2013

 
ዊኪ-መዝገበ-ቃላት የባለ ብዙ ቋንቋው ዊክሽነሪ የአማርኛ ዝርያና የዊኪፒዲያ ነፃው መዝገበ-ዕውቀት እህት መርሃ ግብር ነው። ዓላማውም ሁላችንም በመተባበር አንድ ክፍት ነፃና ህሉም ሰው ያለ ምንም ገደብ ሊጠቀምበት የሚችል መዝገበ-ቃላትን መድረስ ነው። ይህ የእማርኛ ዊኪ-መዝገበ-ቃላት በማርች 23 2006 ተጀምሮ በአሁኑ ሰዓት 205 ገጾችን ይዟል። አንድ ገጽ የአንድ ቃልን ምንጭ፣ ሂደታዊ ታሪክን፣ የቀድሞና ውቅታዊ አጠቃቀምን፣ ተዛምዶን፣ የአጠቃቀም ምሳሌን፣ ተጨማሪ ተጠቃሽ መረጃዎችን፣...ወዘተ ይይዛል፡፡

ይህ መዝገበ ቃላት አማርኛን እንደማዕከላዊ መነሻ ቢያደርግም በአለም ላይ ያሉ ቋንቋዎችን ሁሉ ቃላት ማካተት ይቻላል፡፡ ይህ ከላይ ከላይ ሲመለከቱት አስቸጋሪና መዝገበ ቃላቱን ስርዓት የሚያሳጣው ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ የሚመስለን የባህላዊው ኅትመት ላይ የተመሠረተ የመዝገበ ቃላት አጠቃቀምን ስለምናስብ ነው፡፡ የዓለም ቋንቋዎችን ሁሉ በአንድ መጽሐፍ ላይ እናስቀምጥ ብንል የማይቻል ነው፡፡ ለአስሊ (ኮምፕተር) ምስጋና ይግባውና የዕውቀትና የጊዜ ገደብ ካልሆነ በስተቀር ከላይ የተጠቀሰው አይነት ገደብ እዚህ ላይ አይኖርም፡፡

የሚያውቁት ቋንቋ ካለ፣ ኦሮምኛ፣ ከምባትኛ፣ ኑዌር፣ ዎላይትኛ፣ አገውኛ፣ ትግርኛ፣ ጃፓንኛ፣ ህንድኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኖርዌጅኛ፣....ወዘተ ቃሉን ጽፈው ከየት እንደመጣ፣ ትርጉሙን፣ ተጠቃሽ መረጃዎችን... ወዘተ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ የየትኛውንም ቃል የአማርኛ ትርጉም ለማወቅ የፈለገ ተጠቃሚ ሁሉ ወደዚህ መጥቶ ማየት ይችላል ማለት ነው፡፡ በተለይ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ቋንቋዎች ቃላት እንደ ማከማቻና አንዱ ከአንዱ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሳያ ሊያገለግል ስለሚችል የሚያውቁትን ቃላት በሙሉ በማስገባት ትርጉማቸውን ያስቀምጡ፡፡

የአስሊ(ኮምፒዩተር) ቃላት ትርጉም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የአስሊ መድብለ ቃላት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ICT glossary at AAU ይገኛል፡፡ ይህ ከ2500 ቃላት በላይ የያዘው መድብለ ቃላት የአስሊ ፕግራሞችን ለመተርጎም የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገዋል፡፡ ጥረቱ በቀላሉ የሚሻሻል ሁለት ችግር አለበት፡፡

  1. ተጠሪው (server) በጣም ቀሰስተኛ ስለሆነ ለተጠቃሚው በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህ መስተዋት ገጽ (mirror site) በተለያዩ ክፍለዓለማት በማስቀመጥ ማሻሻል ይቻላል፡፡
  2. ገጹ ላይ የተሰጠው የexel ቅጂ የተጻፈው በተለያየ የፊደል ቅርጽ(font) ከመሆኑም በላይ አንዱ ከአንዱ ጋር ተኳኻኝ (compateble) አይደለም፡፡ በዩኒኮድ ደረጃን የጠበቁ ነፃ ፊደሎች በመጠቀም ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው በሚችልበት ሁነታ ቢዘጋጅ ጠቃሚነቱ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
የአቡጊዳ ታሪክ

የአማርኛ ቋንቋን የምንጽፍበት ፊደላት ታሪክን ከአቡጊዳ በውክፐዲያ ይማሩ።

የአስሊ(ኮምፒዩተር) ቃላት ትርጉም

ይህንን የአስሊ መድብለ ቃላት computer terms glossary አጓዳኝ ሲጫኑት 1500 የሚጠጉ የአስሊ (ኮምፒተር) ቃላትን የእንግሊዝኛ-አማርኛ ትርጉም ረቂቅን ያገኛሉ። ይህን መድብለ-ቃላት ወደ አስሊ መድብለ ቃላት ክፍል በማዛወር ላይ እንገኛለን፡፡ እነዚህ ትርጉሞች ረቂቅ ሃሳቦች እንጂ የመጨረሻ አይደሉም። እርስዎ የተሻለ አማራጭ አለ ብለው ካሉ ይህንን አማራጭ ወይም አማራጮች ከመጀመሪያው ትርጉም ጎን በነጠላ ሰረዝ በመከፋፈል ያስቀምጡት። የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ጊዜ አማራጮቹ ሁሉ ተዘርዝረው ቢገኙ የተሻለውን አማራጭ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመስጠት ያመቻል።


በቅርቡ በማይክሮሶፍት ውጤቶች ላይ የተመረኮዘ ባለ 2828 ቃላት የአስሊ መድብለቃላት በEICTDA ተለቋል። መድብለ ቃላቱ የተሟላና ጥራት ያለው ነው ለማለት ቢያስቸግርም ለተርጓሚዎች እንደመነሻ ሊያገለግል ስለሚችል እዚህ ቀርቧል። በዚህ አጋጣሚ የባለስልጣኑ ተርጓሚዎች፣ ከዚህ ቀደም በባለሙያዎችና ተጠቃሚዎች የተሰሩ ብዙ የትርጉም ስራዎች ስላሉ እንሱን እያዩ ከባለስልጣኑ የሚወጣውን ስራ ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ቢጥሩ ጥሩ ነው። ይህ ከትውልድ ተውልድ የሚተላለፍ ስራ በመሆኑ በማናለብኝነት ጥራት የሌለው ስራ መስራት ጥሩ አይሆንም። ለመጠቀም ያመች ዘንድ ከላይ የተጠቅሰው በዚሁ ውክሽነሪ EICTDA መድብለቃላት ውስጥ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ጥናት ኢኒስቲቱትመዝገበቃላት አስራር ላይ የተመረኮዙ ጥናቶች ላይ ያተኮረ ጉባዔ.......


ማስተዋፅ ይችላሉ!
ይህ መዝገበ-ቃላት የሚፃፈው በፈቃድኛ አስተዋጺዎች ነው። ማስተዋጽ በጣም ቀላልና ማንም ሰው ሊያደርገው የሚችለው ነው። «አርም» የሚለውን በመጠቆም ሥራዎን መጀመር ነው። አንድ ቀይ አጓዳኝ ማለት ገቢ ቃሉ ዊኪ-መዝገበ-ቃላቱ ውስጥ ገና የለም ማለት ነው። አዲስ ገቢ ቃልን በመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ ጽፎ «ሂድ» በማለት መፍጠር ይቻላል። በተጠቃሚነት መመዝገብም ይቻላል። ርዳታ ካስፈለገዎትም ምክር ቤቱን ይመለከቱ:

ሰዋሰው
የዘይቤ መመሪያ

ዊክሽነሪ ዊኪፔድያ አይደለም
ስለዚህ የመዝገበ-ዕውቀት መጣጥፎችን እዚህ ላይ አያኑሩ።


ዊክሽነሪ በሌላ ቋንቋ

ዐረብኛ (العربية)ዳኝሽኛ (Dansk)እንግሊዝኛ (English)ኤስፔራንቶ (Esperanto)ፊንላንድኛ (Suomi)ፈረንሳይኛ (Français)ግሪክኛ (Ελληνικά)ዒዶ (Ido)ኢስላንድኛ (Islenska)ጣሊያንኛ (Italiano)ጃፓንኛ (日本語)ቻይንኛ (中文)ኮሪያንኛ (한국어)ሆላንድኛ (Nederlands)ኖርዌጅኛ (Nynorsk)ፖላንድኛ (Polski)ሩሲያኛ (Русский)ስፓኝ (Español)ስዊድንኛ (Svenska)ጀርመንኛ (Deutsch)