ዋዝንቢት
ዋዝንቢት የትኋን አይነት ነው። የፌንጦና የአንበጣ ዘመድ ነው። ሁለንተናው ትንሽ ለጥ ይላል፤ የረዘሙ አንቴኖችም አሉት።
ዋዝንቢት ታዋቂ የሚሆነው በተለይ ስለ ድምጹ ይሆናል። ይህን ለማሰማት የሚችለው አውራ ዋዝንቢት ብቻ ነው፤ የተባዕቱ ክንፍ እንደ "ሚዶና ሞረድ" የሚመስል ፍርግርግ መሣሪያ አለበትና። ክንፎቻቸውን በማፋተግ ድምፃቸውን ያሰማሉ፤ ዘፈናቸውም በየወገናቸው ይለያያል። ሁለት ዓይነት የዋዝንቢት ዘፈኖች አሉ፤ የጥሪ ዘፈንና የመርቢያ ዘፈን ናቸው። የጥሪ ዘፈን አንስት ይስባልና እጅግ ከፍ ይላል። የመርቢያ ዘፈን አንስቲቱ ስትቀርብ ይጠቅማልና በጣም ቀስ ይላል። አንስት ዋዝንቢት የረዘመ እንደ መርፌም የሚመስል ዕንቁላልም የሚጥል ዕቃ አለባት።
በምድር ላይ 900 የሚያሕሉ የዋዝንቢት ወገኖች ይገኛሉ። ዋዝንቢት በሌሊት የሚነቃ ወደ መሆን ያዘንብላል። ብዙ ጊዜ ለዘመዱ ለፌንጣ ይሳታል፣ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ያሉበት የሁለንተናቸው ቅርፅ ተመሳሳይ ነውና።
በ1963 ዓ.ም. ዶ/ር ዊሊያም ከይድ ምርመራ አድርጎ አንዲት ተባይ ዝንብ ደግሞ በተባዕቱ ዘፈን እንደምትሳብ፤ ዕጯንም እንድታስቀምጥበት ቦታውን ለማወቅ እንደሚጠቅማት አገኘ። የመርባትን ድምጽ በመጠቀም የአስተናጋጇን ቦታ ለምታገኝ የተፈጥሮ ጠላት ይህች መጀመርያ ምሳሌ ሆነች። ከዚያ በኋላ ብዙ የዋዝንቢት ወገኖች ይህችን ተባይ ዝንብ ሲሸክሙ በምድር ላይ ተገኝተዋል።
በ
እስያ በተላይም በ
ቻይና ዋዝንቢት ዝነኛ
ለማዳ እንስሳ ሆኖ እንደ መልካም እድል ይቈጠራል። በአንዳንድ ባሕል ደግሞ እንደ ምግብ ሊበላ ይችላል።