ዋናው ገጽ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዛሬ ማክሰኞጥቅምት 6 ቀን 2005
( 16 ኦክቶበር, 2012 እ.ኤ.አ. )ነዉ።
Icon of three people in different shades of grey.svg
መቅድም                       
መቅድም                       
      ወደ ውክፔዲያ እንኳን ደህና መጡ! ውክፔዲያ ማለት የተለያዩ አገር ሰዎች ተሰባስበው በብዙ ቋንቋዎች የዓለምን ዕውቀት እየመዘገቡ እና እያነበቡ ያሉበት በጣም ታዋቂ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ የጋራ ነው። ማንም ሰው በዚህ መዝገበ ዕውቀት ሊጽፍ ይችላል። እርስዎ ለውክፔዲያ አዲስ ከሆኑ እላይ ለጀማሪዎች የሚለውን አፅቅ ይጫኑና እንዴት እንደሚሳተፉ ይማሩ።

እዚህ ውክፔዲያ ላይ ጽሑፍ ለማቅረብ፡

  • ድፈሪ -- አዲስ ጽሑፍ ለመጀመር ወይንም ያለውን ጽሑፍ ለማስተካከል ምንጊዜም አትፍሪ። ጽሑፍሽ ያልተሟላ፣ ወይንም ያልተጠናቀቀ ቢመስልሽ አትጨነቂ። ጅምር ጽሑፍሽ በተፈለገው ጊዜ ሊስተካክል፣ ሊሻሻል እና ሊጠናቀቅ ይችላል።
  • ተማሪ አስተምሪ -- በማንኛውም የዕውቀት ዘርፍ ለመሳተፍ ይቻላል። ተማሪዎች በጥናታቸው ጊዜ እሚያጠኑትን ትምህርት ተርጉመው በጥቂቱ ቢጽፉ ለጥናታቸው ይረዳቸዋል።
  • ተርጉም -- ጽሑፍ ለማቅረብ የግዴታ ከባዶ መነሳት አያስፈልግም። ከእንግሊዝኛው ውክፔዲያ ወይም ከሌላ ቋንቋ ውክፔዲያም እየተረጎምክ ጽሑፍ ማቅረብ ትችላለህ።
ዜና ውሎ.png
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።    
ታሪክ፡በዛሬው፡ዕለት።    

ጥቅምት ፮ ቀን


Anwar Sadat cropped.jpg
  • ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ስመ ጥሩው የእስራኤል ጄኔራል፤ እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ሚንስቴርነት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ማዕረግ የበቁት ሞሼ ዳያን በተወለዱ በ፶፮ ዓመታቸው በሞት ተለዩ።
Deco pag5.svg
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስልና፡አዳዲስ፡ጽሑፎች።
የዕለቱ፡ምርጥ፡ምስልና፡አዳዲስ፡ጽሑፎች።

Neopithecops zalmora by Kadavoor.JPG The Quaker (Neopithecops zalmora) is a small butterfly found in South Asia and Southeast Asia that belongs to the Lycaenids or Blues family. The underside is white with a series of dark brown to black marginal spots and a post-discal series of disjoint striae. On the hindwing there is a prominent black spot in space 7 near the costa and a much smaller black spot in space 1a. Taken at Kadavoor, Kerala, India

ትኩስ ሻይ አይከን.svgመጨረሻ የቀረቡ 3 ትኩስ መጣጥፎች

Lgo1.png
የመደቦች፡ዝርዝር።                  
የመደቦች፡ዝርዝር።                  
የዕለቱ፡ምርጥ፡ፅሑፍ።
የዕለቱ፡ምርጥ፡ፅሑፍ።

ዕንቁጣጣሽ


አደይ አበባ.JPG

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡

ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ፤ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን /ሰኮንድን/ ሳይቀር እየሰፈሩ/እየቆጠሩ/ ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡ ዓውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ/ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለም ይጠራል፡፡

የ"ዕንቁጣጣሽ" አመጣጥ

ዓመታት ተፈጽመው አዲስ ዓመት ስንጀምር ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዓውደ ዓመት፣ አዲስ ዓመት ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለ ይጠራል፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡

ሁለተኛው የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስታደንቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎች ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኝ በኢየሩሳሌም የማይገኝ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት አስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው፡፡ እርሱም አንድ ነገር ላይ ሰውሮ ሁሉንም ገለጸላት፡፡ ቤተ መንግሥቱንም፣ በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ እጅግ በጣም የከበሩ ዕቃዎችን ሁሉ አስጎበኛት፡፡ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡

ኃይማኖታዊ መሠረት

ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ «የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ

እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጅ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ» ተብሎ በኢሳይያስ እንደ ተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነሥቶ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ» እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ ለኃጢአት ሥርየት እየሰበከ መጣ ብሎ በዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ገልጾታል፡፡

/የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፵፤ [[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ ፵ ቁ ፫ - ፬/፡፡

የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተክርስቲያን አበው የበዓላቱን ድንጋጌ በወሰኑበት ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል የኢትዮጵያ ርዕሰ ዓውደ ዓመት በሚሆን መስከረም ፩ ቀን እንዲከበር በየዓመቱ የዘመኑ መጀመሪያ በእርሱ ስም እንዲጠራ አባቶች ደንግገዋል፡፡ / ድርሳነ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1ጠ 3/ ይህንንም በዓል አባቶቻችን በርእሰ ዓውደ ዓመት ማክበር እንደሚገባ አስበው ያደረጉት ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ሆኖ አይደለም፡፡ ለአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወይም ርእሰ ዓውደ ዓመት «ቅዱስ ዮሐንስ» ይባላል፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር የዓመቱን መጀመሪያ /መስከረምን/ ሲያትት «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው በማለት ያስረዳል፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከመስከረም አንድ ቀን ጀምሮ ቀኑ እየጎደለ ይሔዳል፡፡

ከዚህ በመቀጠል በዓሉ በተለያየ ስያሜ ስለመጠራቱና ትርጓሜያቸውን እንመለከታለን፡፡

ዘመን መለወጫ

አስቀድመን ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ማንነትና የዘመን መለወጫ መግቢያው ላይ በስሙ ስለመጠራቱ ተመልክተናል፡፡ ዘመን መለወጫ ደግሞ ለምን እንደተባለና ለምን መስከረም ወር ላይ እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲህ በማለት ያትታሉ፡፡ ሲያትቱም ብርሃናት/ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱም ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱንም ጠንቀቀው ቢቆጥሩት ፫፻፷፬ ቀናት ይሆናል፡፡ ለዘመን መታወቂያ ይሆን ዘንድ ፀሐይጨረቃ ከዋክብትን ፈጠረ ይላልና /መጽሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፵፱፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ዓለምን ውኃ አጥለቅልቋት ከቆየ በኋላ ዳግመኛ ከነበረው ውኃ የተገለጠችበት ወር «በመጀመሪያም ወር በምድር ታየች የንፍር ውኃው ከምድር ደረቀ» የሚለውን መሠረት አድረገው የአቡሻኽር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስረዳሉ፡፡/መጽሐፈ ኩፋሌ፡ ምዕ ፯ ቁጥር ፩/

በመሠረቱ ዘመን ተለወጠ ሲባል የሚለወጡት ወራቱ ብቻ አይደሉም፡፡ በወቅቱ የሚከሰቱት/የተከሰቱት/ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር /ገጠመኝ/ ሲሆን ወራቶቹ ግን ያው በየዓመቱ እየተፈራረቁ ይመጣሉ፡፡ ዘመን መለወጫ ላይ የሰው ልጆች ሕይወት ሊለወጥ ይገባል፡፡ ተማሪው ተምሮ ወደቀጣዩ ክፍል /ደረጃ/ የሚለወጥበት፣ ገበሬው የክረምትን ወራት በሚገባ ተጠቅሞ የሚቀጥለውን የበጋ ወራት የሚቀበልበት፣ ሠራተኛው የክረምቱን ዝናብ ታግሶ የፀሐይን ወራት የሚቀበልበት ሌላውም እንደዚያ ሆነው ወራቶቹ በዚያ ዘመን ያለው የተፈጥሮ ክስተቶች የሚለወጥበት ዘመን ተለወጠ እየተባለ ይነገራል፡፡


አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ» ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡
[[|]]
Wikimedia-logo.svg
የሥራ፡እህቶች።
የሥራ፡እህቶች።
Wikibar.png
ይጠይቁ፣ ይሳተፉ !!!
ይጠይቁ፣ ይሳተፉ !!!

ስለ ምን ለማወቅ ይፈልጉ ነበር?በዚህ ያቅርቡ።ቀልዶችን እዚህ ላይ ይጨምሩ!

can't see the Amharic font?

Click here to download the Amharic Unicode.


አዲስ ጽሑፍ ለማቅረብ

  • እሚከተለው ሳጥን ውስጥ ሊያቀርቡት ያሰቡትን ጽሑፍ ርዕስ ያስገቡ።
  • ከዚያ፣ «አዲስ አርዕስት ለመፍጠር» የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።
  • በሚመጣው ባዶ ሰሌዳ ላይ ጽሑፍዎን ከከተቡ በኋላ እታች «ገጹን ለማቅረብ» የሚለውን ቁልፍ በመጫን ስራዎን ያጠናቅቃሉ።



የኔ መሣርያዎች

Variants
Actions
የማውጫ ቁልፎች
ጠቃሚ መሣሪያዎች
በሌሎች ቋንቋዎች